የበበቃ ኮፊ ኢስቴት አክስዮን ማህበር ምርት ለመሠብሠብ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

የበበቃ ኮፊ ኢስቴት አክስዮን ማህበር እርሻውን በዘመናዊ መንገድ በማደራጀትና ቴክኖሎጅዎችን በመጠቀም ምርታማነትን ለማሳደግ በመሥራት ለይ ይገኛል፡፡የሠራተኛዉንም ህይወት ለማሻሻል በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፡፡

አሁን ወቅቱ በበበቃ ታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የቡናና ቁንዶ በርበሬ ምርት ለመሠብሠብ መላ ሠራተኛው የአካባቢዉን ማህበረሰብ በማስተባበር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በቀን 28/10/2013 ዓ.ም ምሽት 1፡30 አካባቢ ማንነታቸዉ የማይታወቁና ቁጥራቸው ከ15 እስከ 20 የሚደርስ ታጣቂዎች አብይ 04 ተብሎ በሚጠራው የድርጅቱ እርሻ ላይ የዘረፋ ሙከራ አድርገው በጥበቃ ሠራተኞችና በአካባቢው ነዋሪዎች ከሽፏል::

ይህንን እንቅስቃሴ ለመግታት ከዞንና የወረዳ አመራሮች ጋር በመተባበር የተቀናጀ ስራም የተከናወነ መሆኑን የአክስዮን ማህበሩ  ዋና ሥራ አሰኪያጅ አቶ አብረሃም ማህደር አስረድተዋል፡፡

በጥቅሉ ሲታይ የበበቃ ኮፊ ኢስቴት አክስዮን ማህበር ከምርት ስራው ባሻገር ከምን ጊዜውም በላይ የአካባቢውን ልማት በመደገፍና መሰረተ-ልማቶችን በመገንባት ለአካባቢው ማህበረሰብ ያለውን አለኝታነት በማሳደግ ላይ ይገኛል፡፡ ማህበረሰቡም እርሻውንና ምርቱን እንደራሱ ንብረት በማየት እየጠበቀው ነው፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ በተቃራኒ ዘሐበሻ በሚባል የዩቱዩብ ሚዲያ አርብ ሀምሌ 2/2013 ዓ.ም በተለቀቀ ዘገባ እርሻው በአካባቢው ወጣቶች እንደተወረረና ንብረትም እንደወደመ ተደርጎ ተሰራጭቷል፡፡

ይህ ወሬ መሠረተ-ቢስ የሆነና እውነታውንም ለማረጋገጥ ምንም አይነት ጥረት ሳይደረግ የተለቀቀ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

ይህ መረጃ በተለመደ የማደናገሪያ ሴራ የተቀናበረና የልማት አደናቃፊዎች ህልም እንጂ መሬት ላይ ካለዉ እዉነታ ጋር የተፃረረ መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን::

ሰኢድ መሀመድ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ