የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ እና የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ሶማሌ ተራ አካባቢ በሚገኘው የተስፋ ብርሃን አሙዲ የምግባ ማዕከል ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የማዕድ ማጋራት አካሄዱ፡፡

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በስድሰቱ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የተስፋ ብርሐን የምገባ ማዕከላት ተቋማቸው 6 ሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው በሥነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት በዓልን ድጋፍ ከሚሹ ጋር ማክበር በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡እንዲህ ሆነን እድናከብር በየ ግምባር ያሉ የመከላከያ እና የጸጥታ አካላት በሚከፍሉት የህይወት መስዋእትነት በመሆኑ ክብር ይገባቸዋል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ሁሉም ዜጋ በየተሰማራበት ጀግና ሊሆን እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕም ላደረገው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቹ ስም አመስግነዋል።