የመልካምነት ቀን ለአቅመ ደካሞች መአድ በማጋራት በወዳጅነት ፓርክ ሲከበር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሊቀመንበራችን ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ይሁንታ 5 ሚሊየን ብር ማበርከቱ ተገለጸ፡፡
የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ከኢቲቪ ዜና ጋር በነበራቸው ቃለ-መጠይቅ እንደገለጹት ተቋሙ በዓሉንም አዲስ ከተማ ክ/ከተማ በሚገኘው ተስፋ ብርሐን አሙዲ የምገባ ማዕከል ድጋፍ ከሚደረግላቸው አባላት ጋር እንደሚያከብር ተናግረዋል፡፡