በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማዕድን ዘርፍ “Strategic Planning and Management” ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጠ፡፡

በዘርፉ ውስጥ ለሚገኙ 55 የዋናው ቢሮ ሃላፊዎች፣ የኩባንያዎች ስራ አስኪያጆችና ዲፓርትመንት ሀላፊዎች ከመስከረም 13 እስከ 25/2014 ዓ.ም በመቻሬ ሜዳ የተሰጣቸውን ሥልጠና አጠናቀዋል፡፡ሥልጠናው ከኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን በተለይም የስትራቴጂክ እቅድ አዘገጃጀትና አተገባበር ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ስልጠናው በተግባር ልምምድ የተደገፈና የስትራቴጂክ ሰነዱን በአጭር ጊዜ አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ለመግባት የሚያስችል አቅም መፍጠር ያስችላል ተብሏል፡፡በሥልጠናው መክፈቻ ላይ በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማእድን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዱላ መኮንን ለተሳታፊዎች የሥራ መመሪያም ሰጥተዋል፡፡