በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ለንግድና የአገልግሎት ዘርፉ አመራሮች ሲሰጥ የነበረው የስትራቴጂክ ማኔጅመንትና የሥራ አመራር ለውጥ ሥልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአዲስ የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የረዥም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ግቦችን ነድፎ ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።ኢንቨስትመንት ግሩፑ ካሉት ክላስተሮች መካከል አንዱ የሆነው የንግድና አገልግሎት ዘርፉ በስሩ ወደ 7 የሚጠጉ ካምፓኒዎችን አቅፏል።ከመስከረም 24 2014 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 01 2014 ዓ.ም በቆየው ስልጠና ላይ የተካፈሉት የኪዊንስ ሱፐር ማርኬት፣ አዳጎ ኢምፓርት፣ ትረስት ሴኩሪቲ፣አዲስ ኬቴሪንግ፣ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስና ሰላም የህክምና ማዕከል የተወጣጡ የካምፓኒ አመራሮች ናቸው።ቁጥራቸው 50 ለሚደርሱ በየደረጃው ለሚገኙ የስራ አመራሮች የተሰጠው ስልጠና ዋና አላማ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በመጪዎቹ አምስት አመታት ሊያሳካቸው ያቀዳቸው ስትራቴጂካዊ ግቦችን በካምፓኒ ደረጃ አውርዶ ለማሳካት ታላሚ ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል።በስልጠናው ቆይታቸው የስትራቴጂካዊ እቅድ አዘገጃጀት አነዳደፍ ና ትግበራ ሳይንሳዊ ምንነትና የአመራር ክህሎት ማዳበርን በተመለከቱ ጉዳዬች ላይ ተግባር ተኮር እውቀት ማግኘት መቻላቸው ተመላክቷል።ሥልጠናው የተዘጋጀው በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኮሜርስ ክላስተርና የግሩፑ ማንፋክቸሪንግ ክላስተር የአቅም ግንባታ ዳሬክቶሬት ጋር በጋራ በመተባበር ሲሆን በተለይም የስትራቴጂክ እቅድ አዘገጃጀትና የለውጥ ሂደት አመራር ላይ ያተኮረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገ የአመራርና አደረጃጀት ለውጥ በኋላ በሌሎች ዘርፎችም ይሁን በንግድና አገልግሎት ዘርፍ ኪሳራ ውሥጥ የነበሩ ተቋማት ከፍተኛ የሚባል መሻሻል እያሳዩ መምጣታቸው ተጠቁሟል።የተመዘገበውን ለውጥ በተሻለ መንገድ ውጤታማ ለማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱንና ሁሉም ወደ ተቋሙ ሲመለስ ያገኘውን እውቀት እስከ ታችኛው እርከን እንዲያወርድ እንደሚጠበቅ የንግድና አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሁሴን አህመድ ለተሳታፊዎች አስገንዝበዋል።በሥልጣናው መክፈቻ ላይ የተገኙት አቶ ሁሴን ለተሳታፊዎቹ የሥራ መመሪያም ጭምር መስጠታቸውን ገልጸው መረጃውን ያደረሱን አቶ እንዳልካቸው ግርማ የንግድና አገልግሎት ዘርፍ የማርኬቲንግ ዳሬክተር ናቸው።