ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የጀግና ምልክት የሆነውን ፈረስ ተሸለመ፡፡

የምሥራቅ ሸዋ ዞን አድአ ወረዳ ነዋሪዎች ሽልማቱን ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ያበረከቱት ስለተደረገላቸው መልካም ስራ ለማመስገን መሆኑን በተወካዮቻቸው በኩል ተናግረዋል፡፡ እንደተወካዮቹ ገላጻ ግሩፑ አይተውት የማያውቁትን ብርሃን ሰጥቷቸዋል፡፡በወረዳው ከ2 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት በመስራት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡“ይህን ያደረገልን ተቋም ጀግናችን ነው፡፡በባህላችን ደግሞ የጀግና ምልክት ፈረስ ነው፡፡ በመሆኑም ይህን ስጦታ ይዘን አዲስ አበባ ድረስ መጥተናል::” ብለዋል፡፡ሽልማቱን የተረከቡት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው ስለተበረከተው ስጦታ አመስግነዋል፡፡ በቀጣይም ማህበረሰብን ለሚደግፍ በጎ ነገር ሁሉ ተቋማቸው ከፊት ቀድሞ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ሰኢድ መሀመድ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት