ሚድሮክ ኢትዮጵያና ማሪዮት ኢንተርናሽናል አፍሪካ ዩኒየን ግራንድ ሆቴልን ጨርሶ ለማስተዳደር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ፣ህዳር 3፣ 2014 ዓ.ም (ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ) ሚድሮክ ኢትዮጵያና ማሪዮት ኢንተርናሽናል አፍሪካ ዩኒየን ግራንድ ሆቴልን ጨርሶ ለማስተዳደር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ አጠገብ ያለውን የሚድሮክ ኢትዮጵያ ንብረት የሆነውንና አፍሪካ ዩኒየን ግራንድ ሆቴል የሚባለውን ሆቴል የማሪዮት ኢንተርናሽናል ጨርሶ ለማስተዳደር ነው ስምምነቱ የተደረገው፡፡

 በሚድሮክ ኢትየጵያ በኩል ስምምነቱን የተፈራረሙት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ “ከማሪዮት ኢንተርናሽናል ጋር ለረጅም ጊዜ  መስራታችን ባስገኘልን የጋራ ጥቅም ምክንያት የዌስቲን ብራንድ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ከፍተኛ ፍላጎት አድሮብናል” ብለዋል።

 በምስራቅ አፍሪካ የማሪዮት ኢንተርናሽናል የሎጅንግ ዴቨሎፕመንት ዳይሬክተር ያሲን ሙንሺ በበኩላቸው “ይህ አስደናቂ ፕሮጀክት ከሚድሮክ ጋር ያለንን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና በኢትዮጵያም ያለንን አሻራ ከፍ የሚያደርግ በመሆኑ ደስተኞች ነን” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ይህ ሥምምነት ከሁለቱ አካላት ተጠቃሚነት ባሻገር ለሆቴል ዘርፉም ሆነ ለኢትዮጵያ ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑም በስምምነቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡